top of page
Search
Writer's pictureAlem Nida

Paving the path to a brighter future

Updated: Jun 21, 2020


ጥቂቶች ስለወደፊቱ የጉራጌ እጣፈንታ ያሳሰባቸውና ጥርጣሬ ያደረባቸው ሰዎች መልስ ቢኖረኝ ከመቼውም በላይ የጉራጌ ተወላጆች በአንድነት ችግሮቻችንን ለመወያየት እንዲሁም መፍትሄ ጭምር ለመፈለግ ከጉራጌ መንገዶች ምስረታ ቀጥሎ ይህኛው ጉዳዩ መጀመሪያው ነው ብዬ አገመተለሀኘ:: ያለው መነሳሳት ደግሞ ቀጣይነት እንዲኖረው ምኞት ብቻ ሳይሆን በአካባቢው ተወላጅነት ትልቅ ሃላፊነት አለብን ብዬ እገምታለሁ:: የክልል አቀንቃኝ አይደለሁም ነገር ግን አሁን ባለው አጣብቂኝ ህዝባችንን መብቱንና የሶሻል እንዲሁም ፖለቲካል መፍትሄው አብረን መወጣት አለብን የሚል ግምት አለኝ:: ዝም በማለታችን የተወሰደብንን ማስተዋል ይገባናል:: አባቶቻችን እንዲሁም ጫማ እየጠረጉ ያሰባሰቡትን ሳይቀሩ መንገድ ለማሰራት ያደረጉት አስተዋጽኦ እንዲያው በከንቱ እንዲቀር ኢህአዴግ የመንገዱን መዋቅር ሰባብሮ ዛሬ ለአለም ምሳሌ ሊሆን የሚችለውን ራስ እገዛ ድርጅት ከጨዋታ አስወጥተዋል :: በወልቂጤ ሊሰራ የነበረውን ሆስፒታል ገንዘብ ዘርፈዋል:: ዝምታ ዋጋ ያስከፍላል::

ዛሬ ልናደርግ የምንችለው ቢኖር enough is enough ብለን በአንድነት ያለንን ልዩነቶች አስወግደን ችቦ መሆን ይኖርብናል:: No one should insult our intelligence anymore indeed!

ጉራጌዎች ከማንኛውም አንስተ አብቃይ ብሄረሰቦች የጠነከረ ባህል ያለን የቤት አሰራሮችን በውበት የተገነባ የመንገድ አሰራሮችን የትም የሚያገኙ የእርሻ ዘዴዎችን እንዲሁም የፍትህ ተቋማት የjoka የመሰሉትን የዳበረ ሶሻል ስትራክቸር ያለው የተከበረ ህዝብ ነው::

ታዲያ ቋንቋችንን ለማዳበር የጥናትና የባህል ተቋማት ለማዳበር አካባቢያችንን በኢኮኖሚ በፍትህና ሶሻል ተቋማት እራሳችንን ከማስተዳደር ሌላ አማራጭ የለንም:: አገር ቤት ያለው የጉራጌ ህብረተሰቡና በውጭው አለም የተሰበሰብነው የጉራጌ ልጆች የሚያስፈልገን መተማመን ትብብር እንዲሁም commitment ናቸዉ:: ከዚያ በሁዋላ የሚሆነው በአንድነት ማድረግ ያለብን ግማሹን ልቦናችንን ለዚያ ምስኪን ህዝብ አለንልህ ልጆችህ ብለን ስትራቴጂ አውጥተን የጎደለውን ማሟላት ነው:: በሁሉም አቅጣጫ የተማረ አሳቢነት የተሞላው እንኳን ለኢትዮጵያ ይቅርና በአለም ዙሪያ የመከበርና እውቅና ያገኙ ወንድሞችና እህቶች አሉና ከእንግዲህ ብቃት እንዳሉና ችሎታው በተግባር መዋያ ጊዜ ነው::

A team becomes more than just a collection of people when a strong sense of mutual commitment creates synergy, thus generating performance greater than the sum of the perfect of its individual members.




53 views0 comments

Comentarios


bottom of page